አዲስ አበባ እና የቻይናዋ ቾንቺን ከተማ የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚጠናከርበት ጉዳይ ዙሪያ ውይይት ተደረገ
************************
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት ከቻይናዋ የቾንቺን ከተማ አስተዳደር ኮንግረስ ሊቀመንበር ዣዎ ሺቺንግ ጋር የሁለቱ ከተሞች የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚጠናከርበት ጉዳይ ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
የቾንቺን ከተማ አስተዳደር ኮንግረስ ሊቀመንበር ዣዎ ሺቺንግ እና የልዑካን ቡድናቸው አዲስ አበባ ከበርካታ የቻይና ከተሞች ጋር በቅርበት እንደምትሠራ ማስታወሳቸውን ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ጠቁመዋል።
በዚህም “ከቾንቺን ከተማ ጋርም የእህትማማችነት ስምምነት እንድትፈራረም እና ግንኙነታችን ይበልጥ እንዲጠናከር ያላቸውን ፍላጎት መነሻ በማድረግ በኢኮኖሚ ትብብር፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በቴክኒክ እና ሞያ፣ በነፃ የትምህርት ዕድል እንዲሁም በባህል እና ቱሪዝም ዘርፎች ላይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የእህትማማችነት ስምምነት ለመፈራረም ተስማምተናል” ሲሉ ገልጸዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook