ሦስተኛው ኢትዮ-ቻይና ሳይንስና ቴክኖሎጂ የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ ተካሄደ።
==========================
ሦስተኛው ኢትዮ-ቻይና ሳይንስና ቴክኖሎጂ የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ የሁለቱም ሀገራት ሚኒስትሮች እና የየሀገራቱ ከፍተኛ ልኡካን ቡድን በተገኙበት በዛሬው እለት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተካሂዷል።፡፡

በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ኢትዮጵያና ቻይና ያለፉት አመታት የጋራ ትብብር ማዕቀፎችን በመገምገም በቀጣይ አምስት አመታት በአዳዲስ ዘርፎች ላይ አብረው ለመስራት የሚያስችሉ የጋራ ስምምነቶች የሁሉቱ ሃገራት አመራሮች የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

በዝግጅቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ሀገራችን ለሳይንሳዊ ምርምር፣ ለቴክኖሎጂ ፈጠራ እና ለዕውቀት ሽግግር ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ፖሊሲዎችን እና ስትራቴጂዎችን በመቅረፅ እየሰራች ያለች ሲሆን እነዚህ ስራዎችን ከግብ ለማድረስ ይህ መድረክ ወሳኝ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡

ሀገራችን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ሀይልን በመጠቀም በኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት እድገት ላይ ከፍተኛ ለውጥ አሳይታለች ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ ይህን ትብብር በማጠናከር በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በትምህርትና ስልጠና እንዲሁም በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት አጠናክረን በመስራት ዘርፉን ለኢኮኖሚያዊ ለውጥ ያለውን ፋይዳ መጠቀም ይኖርብናል ብለዋል።

በቻይና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምክትል ሚኒስትር ሊን ዢን (Vice Minister Ms. Lin Xin) ይህ ሦስተኛው ኢትዮ-ቻይና ሳይንስና ቴክኖሎጂ የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ የሁለቱም ሀገራት ግንኙነት በማጠናከር በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር መሰል ጉዳዮች በጋራ እንዲሰሩ ያደርጋል ብለዋል፡፡

በተካሄደው ስምምነት በሁለቱ ሀገራት ያሉ ተመራማሪዎች እና ሳይንቲስቶች መካከል ያለውን ትብብር እና ልውውጥ በስልጠናዎች፣ በአጫጭርና ረጃጅም ትምህርቶች፣ በወርክሾፖች፣ በጋራ የምርምር ፕሮጀክቶች ፣ የጋራ ላብራቶሪዎችን በማቋቋም እና የኢኖቬሽንና የስራ ፈጠራ ትብብርን በማመቻቸት የጋራ ግንኙነትን ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነው፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook