ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ከቻይናው ግዙፍ የግብርና እና ኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች አምራች ኩባንያ ከሆነው ZOOMLION ጋር የግብርና ማሽነሪዎች ዘርፍ በጋር ለመሰራት የሚያስችል የትብብር ስምምነት በቻይና ቻንግሻ ከተማ ተፈራርሟል።
በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት ክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ግብርና ሚኒስትር ዶ/ር ግርማ አመንቴ አገራችን ባለፉት አመታት ግብርናን ለማዘምን ከፍተኛ ትኩርት ስጥታ እየሰራች እንደምትገኝ ገልጸው፣ አንዱ የትኩረት አቅጣጫ የግብርና መካናይዜሽን መሆኑን አስረድተዋል። በዚህም የስምምነቱ ሰነዱ በመጀመሪያው በከፊል የተገጣጠሙ የእርሻ መሣሪያዎችን በማስመጣትና ቀሪ የገጠማ ሥራዎችን በሀገር ውስጥ በማጠናቀቅ ለገበያ ማቅረብ፥ ሲቀጥል የእርሻ መሣሪያዎችን አስመጥቶ በኮርፖሬሽኑ ማዕከል ሙሉ በሙሉ መገጣጠምን እንደሚያካተት ተገልጿል።
በስምምነቱ የሰንዴ፣የበቆሎ፣የሩዝ እና ሌሎች የግብርና ምርቶችን ለመሰብሰብ የሚያገለግሉ የእርሻ መሣሪያዎችን የሚካተቱ ሲሆን፣ ክቡር ሚኒሰትሩ አያይዘውም አገራችን በግብርና ዘርፍ ያላትን ሰፊ የኢንቨስትመንት እድሎችን ለመድረኩ አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የልዑካን ቡድንን የመሩት የግብርና ሚኒስትር እና የኮርፖሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ግርማ አመንቴ በቻይና ሁናን ክልል ዋና ከተማ ቻንግሻ የሚገኘውን ZOOMLION የዘመናዊ የኢንዱስትሪ ከተማን በጎበኙበት ወቅት ለአገራችን ነበራዊ ሁኔታ አመቺ የሆኑ የግብርና ማሸነሪዎችን ከነመገጣጠሚያቸው በማምረት ብሎም ለውጭ ገበያ በማቅረብ ኩባንያው በኢንቨስትመንት ዘርፍ እንዲሰማራ ጥሪ አቅርበዋል።
በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ ZOOMLION በመወከል የድርጅቱ ምክትል ፕሬዜዳንት Mr. Wang Yongxiang እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች የተገኙ ሲሆን፣ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ክፍሌ ወሌደማርያም ኮርፖሬሽናቸውን በመወከል የትብብር ስምምነቱን ፈርመዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook