የኢትዮጵያዋ ባህርዳር እና የቻይናዋ ዱጃንየ ከተሞች የእህትማማችነት ስምምነትን ተፈራረሙ::
====================================

በአዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሚመራው የልዑካን ቡድን በቼንዱ እያደረገ ባለው የስራ ጉብኝት ላይ የባህርዳር እና ዱጃንየ ከተሞች ዛሬ የእህትማማችነት ስምምነት ተፈራርመዋል::

የባህርዳር ከተማ ከንቲባ ጎሹ እንዳለማው እና የዱጃንየ ከተማ ከንቲባ ጃንያ ዳን ስምምነቱን የተፈራረሙ ሲሆን በቀጣይ ሁለቱ ከተሞች በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በቱሪዝም፣ በፓርክ ልማትና አስተዳደር እንዲሁም በአረንጏዴ ልማት ስራዎች ዙሪያ ለመተባበር ተስማምተዋል::

በተጨማሪም በከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራው የልዑካን ቡድን የቻይና የፓርክ ከተማ ተብላ በምትታወቀው ቼንዱ ከተማ የተለያዩ ፓርኮችን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል::

በጉብኝቱ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ፣ ም/ከንቲባ ጃንጥራር አባይ ፣ የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ኃላፊ ሞገስ ባልቻ ፣ የባህርዳር ከተማ ከንቲባ ጎሹ እንዳለማው፣ የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ መኩሪያ መርሻዬ እንዲሁም ሌሎች ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል እና ከኢትዮጵያ ከተሞች ጋር በትብብር ለመስራት የቻይና ከተሞች ላሳዩት ተነሳሽነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል::

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook