አምባሳደር ተፈራ ደርበው በ2023 China-Africa forum on Optical Character Recognition and Natural Language Processing ላይ ተሳተፉ
==========================================
ሰኔ 29/2015 በውሃን በተካሄደው በ2023 China-Africa forum on Optical Character Recognition and Natural Language Processing ባደረጉት ንግግር አፍሪካ የካበተ ባህልና ቋንቋ ባለቤት ስትሆን ይህንን ሀብት በቴክኖሎጂ በመደገፍ ማለትም በOCR Optical Character Recognition and NLP Natural Language Processing በመጠቀም በአፍሪካ ቋንቋዎች ውስጥ ያሉትን እውቀቶች በማውጣት ለማህበረሰቡ ጥቅም ማዋል እንደሚገባ አንስተዋል።
የባህርዳር ዩንቨርስቲ ፕሪዝዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኝ ዩንቨርስቲው በተለይ በቴክኖሎጂ ዘርፍ እያደረገ ስላለው ምርምር ያብራሩ ሲሆን በተለይ በOCR Optical Character Recognition and NLP Natural Language Processing ላይ ከቻይና ዩንቨርስቲዎች ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እናዳለውና ለዚሁም ማሳያ ከሀንጆ ዩንቨርስቲ ጋር የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸውን አንስተዋል።
በመጨረሻም በአፍሪካ ቋንቋዎች በቴክኖሎጂ ለመደገፍ ከፍተኛ ምርምር እያደረጉ የሚገኙት ኢትዮጲያዊው ዶ/ር ወንድሙ የቻይና ዩንቨርስቲዎች የአፍሪካ ቋንቋዎችን ለመደገፍ የሚያደርጉትን ጥረት የአፍሪካ ዩንቨርስቲዎች በቅርበት መከታተል እና አብሮ በመስራት ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ያለቸውን ልምድ አካፍለዋል።