የኢትዮጵያና የቻይና ኢንቨስትመንት ፎረም በሻንሀይ ተካሄደ
============================
በቻይና ሻንሀይ ከተማ ጥቅምት 8 ቀን 2016 በቻይና የኢፌዲሪ ኤምባሲና በተባባሪ የቻይና ካምፓኒዎች አማካይነት የተዘጋጀና ከ300 በላይ የቻይና ካምፓኒዎች የተሳተፉበት የኢትዮጵያና የቻይና የኢንቨስትመንት ፎረም ተካሄደ።
በፎረሙ ላይ የኢፊዲሪ ገንዘብ ሚኒስትር፣ የማዕድን ሚኒስትርና የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር አገራችን ትኩረት በምትሰጣቸው ዘርፎች ፣ አገራችን ያላትን ዕምቅ የማዕድናት አቅም እና ለኢንቨስትመንት ያላትን ምቹ ሆኔታ አብራርተዋል።
ተሳታፊ የነበሩ የቻይና ካምፓኒዎችም በነዚሁ የትኩረት መስኮች ላይ ፍላጎት እንዳላቸው በመግለፅ በቀጣይ ከኤምባሲው ጋር በመተባበር ለቅድመ ኢንቨስትመንት ጉብኝትና መዋዕለ ንዋያቸውን በኢትዮጵያ ለማፈሰስ ፍላጎታቸውን የገለፁ ሲሆን እንዲብራሩላቸው የሚፈልጓቸውን ሀሳቦች በጥያቄና መልስ በማቅረብ በቀጣይ ከኤምባሲው ጋር ትስስር የሚፈጥሩበት የአሰራር ስርዓት በመፍጠር ፎረሙ ተጠናቋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook