ክቡር አምባሳደር ተፈር ደርበውበቻይና ቻንግሻ ከተማ ለሶስተኛ ጊዜ እየተካሄደ የሚገኘው የቻይና-አፍሪካ የንግድ እና ኢኮኖሚ ኤክስፖአንዱ አካል የሆነው ቻይና ዩንግጆ የደረቅ ወደብ ኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ኮንፍረንስ ላይ ተሳትፎ በማድረግ ስለ ኢንትዮጵያ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች ገለጻ አድረገዋል።
ኢትዮጵያ እና ቻይና ዘርፈ ብዙ የትብብር መስኮች ላይ በቅርበት የሚሰሩ ጥንካራ ወዳጅ አገር መሆናቸው የገለጹት አምባሳደሩ የቻይና ኩባንያዎች በአገራችን በመሰረት ልማት ዘርጋታ እንዲሁም በማምረቻ ኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ ነቁ ተሳትፎ ያላቸው መሆኑ አስረድተዋል። ክቡር አምባሳደሩ በመንግስት በኩል ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለመፍጠር እየተደረጉ የሚገኙ የማሻሻያ ስራዎችን በመድረኩ ያስረዱ ሲሆን፥ በተመረጡ ቀዳሚ የኢንቨስትመንት መስኮችም ላይ አገራችን ያላትን ሰፊ የኢንቨስትመንት አቅም እና የቢዝነስ እድሎችን በሰፊው አብራርተዋል።
ከፕሮሞሸን መድረኩ ቀደም ብሎ ክቡር አምባሳደሩ በቻይና ሁናን ግዛት የዩንግጆ ከተማ የኮሞኒስት ፓርቲ ማዕካላዊ ኮሚቴ ዋና ጸሀፊ እንዲሁም ከከተማዋ ከንቲባ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር በአገራችን እና በከተማው በማካከል በንግድ፥ ኢንቨስትመንት እና የተቋማት ትስስር በቅርበት ለመስራት የሚያስችሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
የቻይና አፍሪካ የትብብር ማዕቀፍ(FOCAC) አንዱ አካል የሆነው የቻይና-አፍሪካ ንግድ እና ኢኮኖሚ ኤክስፖ ለሶስተኛ ጊዜ በቻንግሻ ከተማ እየተካሄደ ሲሆን አገራችንን ጭምሮ የበርካታ አፍሪካ አገራት ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛል።