ኢምባሲው በጃንግሱ ዩንቨርስቲ በተካሄደው አለምአቀፍ የባህል ፌስቲቨል ላይ ተሳትፎ አደረገ
===================================
ቅዳሜ ሚያዚያ 12 ቀን 2016 ዓ.ም በጃንግሱ ግዛት በሚገኘው ጃንግሱ ዩንቨርስቲ ለ14ተኛ ጊዜ በተካሔደው አለምአቀፍ የባህል ፌስቲቨል ላይ የኢ.ፊ.ዲ.ሪ ኢምባሲ ተወካይ ተሳትፎ ያደረገ ሲሆን በፌስቲቨል ላይም የኢትዮጵያንና የቻይናን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ላይ ያተኮረ ንግግር ተደርጓል።
በፌስቲቨሉ ላይ ከ45 አገራት በላይ ተማሪዎች አገራቸውን ያስተዋወቁ ሲሆን የኢትዮጵያ ተማሪዎችንም የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግቦችን በማዘጋጀት፣ ቡና በማፈላት እና ታሪካዊ የቱሪስት መስእቦችን የሚስተዋውቁ ፓስተሮች በማዘጋጀት ኢትዮጵያን ለማስተዋወቅ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ዩንቨርስቲው ውስጥ ለሚማሩ ተማሪዎች ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን ተማሪዎች በትምህታቸው ወቅት የሚያጋጥማቸው ችግሮችን ለመፍታት ኢምባሲው አስፈላጊውን ድጋፍ እንሚያደርግ የተገለፀ ሲሆን ተማሪዎችም ለአገራቸው የሚጠቅም እና መሬት ላይ ሊተገበር የሚችል የምርምር ስራዎች ላይ እንዲሳተፉ እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ የራሳቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ መግባባት ላይ የተደረሰ ሲሆን በሚቀጥለው አመት በሚካሄደው ፌስቲቨል አገራቸውን ከዚህ በላይ ለማስተዋወቅ ዝግጆ መሆናቸውን ገልፀዋል::