ክቡር አምባሳደሩ Wenzhou Nixin Trading Co.,LTD ከተባለ ኩባንያ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አደረጉ፣
==================================
በቻይና የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር አምባሳደር ተፈራ ደርበው በወረቀት ማምረት መስክ ከተሰማራ Wenzhou Nixin Trading Co.,LTD ከተባለ የቻይና ኩባንያ ፕሬዚዳንት Mr. Li Shu Fu ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

የውይይቱ ዓላማ የኩባንያው ፕሬዚዳንት የመሩት ልዑካን ቡድን እ.ኤ.አ. ከማርች 21 እስከ 28 ቀን 2024 በሀገራችን የቅድመ-ኢንቨስትመንት ጉብኝት አድርጎ ከተለያዩ የመንግስት መ/ቤቶች ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርጎ መመለሱን ተከትሎ ኩባንያው በተቻለ ፍጥነት ወደ ስራ በሚገባበት ሁኔታ ላይ መምከር ነው፡፡

ኩባንያው በሀገራችን በ80 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ግዙፍ የወረቀት ማምረቻ ፋብሪካ ለመገንባት አስፈላጊውን ቅድመ-ዝግጅት እያደረገ ሲሆን፣ ኩባንያው ሥራ ሲጀምር ለበርካታ ዜጎቻችን አዲስ የስራ ዕድል ከመፍጠሩም ባሻገር ሀገራችን ከውጭ ሀገራት ወረቀት ለማስገባት የምታወጣውን የውጭ ምንዛሬ ያስቀራል፡፡
Mr. Li Shu Fu በሀገራችን ስራ ለመጀመር በመንግስት በኩል እንዲደረግላቸው ያቀረቡአቸውን ጥያቄዎች በተለይም የመሬት እና የኤልክትሪክ ኃይል አቅርቦት ጥያቄ ለመመለስ መንግስት ቁርጠኛ እንደሆነ ክቡር አምባሳደሩ አረጋግጠዋል፡፡ በዚሁ መሠረት የኩባንያው ልዑካን ቡድን የኢንቨስትመንት ሂደቱን ለመጀመር በሀገራችን ሁለተኛ ዙር ጉብኝት እንደሚያደርግ ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook