በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት አዳነች አቤቤ የተመራው ልኡካን ቡድን በቻይና ሻንሀይ ከተማ እያደረገ ያለውን ጉብኝት የቀጠለ ሲሆን፣ የሻንሀያ ከተማ ከንቲባ ልኡካን ቡድኑን በመቀበል በጽ/ቤታቸው ውጤታማ ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይቱም በአዲስ አበባና በሻንሀይ ከተማ መካከል የእህትማማች ከተሞች ሰምምነት እንዲፈረም እና ሁለቱ ከተሞች ያላቸውን ሁሉን አቀፍ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሽጋገር ተስማምተዋል፡፡

በዚህም የሻንሀይ ከተማ ከንቲባ አዲስ አበባን እንዲጎበኙ ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ግብዣ አቅርበዋል፡፡ በመቀጠል በሻንሀይ ከተማ የመጀመሪያው የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ መሰብሰቢያ ሙዚየም፣ የከተማው የትራንስፖርት ቢሮ፣ በሻንሀይ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኘው በቴከኖሎጂ የዘመነ ያንግሻን ፖርትን እና የከተማው ቆሻሻ ማጣሪያ ፍብሪካ ጎብኝተዋል። የአገራችን ልኡካን ቡድን በጉብኝቱ ከፍተኛ የዲፕሎማቲክ ስራ የተሰራበት እና ዘመናዊ ሁሉን አቀፍ የከተማ ልማት እና ፈጣን እድገት ለማምጣት ትልቅ ተሞክሮ አግኝተውበታል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook