መጋቢት 9 ቀን 2016 ዓ.ም.፣ ክቡር የሚሲዮኑ መሪ አምባሳደር ተፈራ ደርበው የቻይና ማሽነሪ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዋና ፕሮጀክቶችን ጎብኝተው ከኩባንያው ዋና ስራ አስኪያጅ Mr.Fang Yanshui ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይቱ ወቅት Mr.Fang Yanshui ኩባንያው በኢትዮጵያ በኮንስትራክሽን፣ በታዳሽ ኃይል እና በማዕድን ዘርፎች ኢንቨስት ለማድረግ ያለውን ዕቅድ ያቀረቡ ሲሆን፣ ክቡር አምባሳደሩ ኩባንያው በሀገራችን ኢንቨስት ለማድረግ በሚኖረው እንቅስቃሴ ሁሉ የኤምባሲውና የመንግስት ድጋፍ እንደማይለየው አረጋግጠውላቸዋል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook