ኤምባሲያችን ከኢትዮ-ቻይና የወዳጅነትና ትብብር ኮሚቴ ጋር በመተባበር Jilin እና Anhui ከተባሉ ከቻይና ፕሮቪንሶች በሀገራችን የቅድመ-ኢንቨስትመንት ጉብኝት እንዲያደርጉ ለመለመላቸው ልዑካ ቡድን አባላት የቅድመ-ጉብኝት ውይይትና ሽኝት ፕሮግራም አካህዷል፡፡ የልዑካን ቡድኑ አባላት በአጠቃላይ 48 ሲሆኑ፣ በዛሬው ዕለት ከJilin የፕሮቪንስ ለተወጣጡ ለ27 አባላት የሽኝት ፕሮግራም ተደርጓል፡፡ እ.ኤ.አ. ዲሴምበር 12 ቀን 2023 በተመሳሳይ መልኩ ከAnhui ፕሮቪንስ ለተወጣጡ 21 አባላት የውይይትና ሽኝት ፕሮግራም ተመቻችቷል፡፡
የጉብኝቱ ዓላማ ከተለያዩ ከመንግሰት የስራ ኃላፊዎች ጋር ተገናኝተው በኢንቨስትመንትና ንግድ ዘርፎች በሀገራችን ስላሉ ዕድሎች ውይይትና ጉብኝት በማድረግ ወደ ሥራ ለመግባት ነው፡፡ ልዑካን ቡድኑ በሀገራችን የሚያደርገው የቅድመ-ኢንቨስትመንት ጉብኝት የተሳካ እንዲሆን ኤምባሲያችን ከዋና መ/ቤታችን ጋር በቅርበት እየሰራ ይገኛል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook