የኢፌዲሪግብርና ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ግርማ አመንቴ ለ3ኛ ጊዜ በሁናን ክፍለ ሀገር፣ በቻንግሻ ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው የቻይና አፍሪካ የኢኮኖሚና የንግድ ኤክስፖ አካል በሆነው በከፍተኛ ልዑካን ደረጃ በተዘጋጀው የቻይና አፍሪካ በግብርና የምግብ እሴት ሰንሰለት ትብብር መድረክ ላይ ተሳትፎ አድርገዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ በውይይቱ ወቅት ግብርና ለኢትዮጵያ ከፍተኛውን የአገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት የሚይዝ መሆኑን እና ትኩረት ከሚሰጣቸው ዘርፎች ዋናው መሆኑን ገልፀዋል። ከዚሁ ጋር በማያያዝ ምርታማነት ላይ ያተኮሩ በርካታ ስራዎች አየተሰሩ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በዘመናዊ መሳሪያዎች መጠቀም፣ እሴት የተጨመረባቸው ምርቶችን በማዘጋጀት ኤክስፖርት ማድረግ የሚጠቀሱ ናቸው።
ክቡር ሚኒስትሩ በመቀጠልም የግብርና ዘርፉን ለማዘመን ከሚሰሩ ስራዎች በዘርፉ ለመሰማራት የሚፈልጉ ባለሀብቶችን መሳብ አንዱ ሲሆን ለዚህም መሬት፣ የውሀ ሀብት፣ የሰው ሀይል፣ ታዳሽ ሀይል፣ ትልቅ የገበያ ዕድል፣ ለግብርና ስራ የሚውሉ ግብአቶችና ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድሎች መኖራቸውን በመግለፅ ለቻይና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ መዋለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪያቸውን
አስተላልፈዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook