በቻይና የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተፈራ ደርበው የSINOMA International ሊቀመንበር እና የCNBM Limited ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት Mr. Liu Yan እና የስራ ባልደረቦቻቸው ጋር በአገራችን በዘርፉ ኢንቨስት በሚደረግበት ዙሪያ ቤጂንግ በሚገኘው የኩባንያው ዋና ጽ/ቤት ተገኝተው ውይይት አድርገዋል፡፡ ክቡር አምባሳደር በንግግራችው SINOMA በአገራችን ባሉት የሲሚኒቶ ፋብሪካዎች ከዲዛይን ጀምሮ በግንባታ ረገድ ላበረከተው አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበው በአገራችን ካለው የግንባታ ስፋት አንጻር የሲሚንቶ ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡
አምባሳደር ተፈራ አያይዘውም ኩባንያው በአገራችን ያለውን ከፍተኛ የሆነ የሲሚኒቶ ፍላጎት ግምት ውስጥ በማስገባት በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ ቢሰማራ የጋራ ተጠቃሚነቱ ሰፊ መሆኑን ጠቁመው በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 18 – 20/2015 በሚካሄደው የኢንቨስትመንት ፎረም ተሳተፎ ማድረግ እንዲችሉ ጥሪ አቅርበውላቸዋል፡፡
Mr. Liu Yan በበኩላቸው ለአንድ አገር እድገት ሲሚንቶና ብረት ወሳኝ ግብዓቶች መሆናቸውን ጠቁመው ዘመኑ ያፈራውን ምርጥ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ለአየር ንብረት ለውጥ አሉታዊ ተጽእኖ የማይኖረው ፋብሪካ በኢትዮጵያ ለመገንባት ሃሳቡ ያላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ኩባንያው በኤምባሲው የቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው በኢንቨስትመንት ፎረሙ የሚሳተፍ ቡድን የሚልኩ መሆኑን ግልጸዋል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook