በChina ITB 2024 ላይ ተሳትፎ ተደረገ
===========================================
የቤጂንግ ኢትዮጵያ ኤምባሲ በቻይና ከሚገኙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር ከሜይ 27 እስከ ሜይ 29 ቀን 2024 ድረስ እየተካሄደ በሚገኘው በChina ITB 2024 የቱሪዝም ፕሮሞሽን ኤግዚቢሽን ላይ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ይገኛል። በእግዘዚቢሽኑ ላይ የአገራችንን የቱሪዝም መስህቦችን የማስተዋወቅ ስራ የተሰራ ሲሆን የቱሪዝም ድርጅቶች በአገራችን stopover ቱሪዝም ላይ እንዲሳተፉ በET Holiday ግብዣ የተደረገላቸው እና ቀጣይ ግንኙነትን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የመረጃ ልውውጥ ተደርጓል።
በኤግዚቢሽኑ ላይ የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽንም የአገራችንን የቱሪዝም መስህቦች የማስተዋወቅ ስራ እየስራ ይገኛል። በተጨማሪም የአገራችን ባህላዊ ውዝዋዜዎችንና የቡና ስነስርአት ማስተዋወቅ ተችሏል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook