በክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተማራ ከፍተኛ የአገራችን ልኡካን ቡድን በቻይና ጉብኝት ለማድረግ ሻንሀይ ከተማ የገባ ሲሆን፣ በቻይና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር ተፈራ ደርበው ኤርፖርት በመገኘት ልኡካን ቡድኑን ተቀብለዋል፡፡ በልኡካን ቡድኑ ውስጥ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ፣ አቶ ሞገስ ባልቻ እንዲሁም የባህርዳር ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ ጎሹ እንዳለማው፣ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ክቡር መኩሪያ መርሻዬ እና የከተማ የፕሮጀክት ኤክሰፐርቶች የተካተቱበት ነበር፡፡ በዛሬው እለት በሻንሀይ ከተማ የሚገኘውን የከተማ ፕላን እግዚቢሽን ማዕከል፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ህዋዌ ቴክኖሎጂ ቢሮ ጎብኝተዋል፡፡ በዚህም ልኡካን ቡድኑ ከተማን ለማዘምን እና ፈጣን የከተሞች እድገት ለማስመዝገብ የሚያስፈልጉ የእቅድ፣ የትግበራ እና ሁሉን አቀፍ የእድገት አቅጣጫዎችን የተማሩበት እና ልምድ የቀሰሙበት ከመሆኑም በላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ በቀጣይ በአገራችን ከተሞች ላይ ለሚሰሩ ስራዎች ተነሳሽነትን የፈጠረ ጉብኝት ሆኗል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook