በኤምባሲያችን ምክትል ሚሲዮን መሪ የተመራ ልዑካን ቡድን በሁቤ ፕሮቨንስ የስራ ጉብኝት በማካሄድ በውሀን ከተማ በተካሄደ በChina-Nordic Economic and Trade Cooperation Forum እና Hubei-Nordic Economic and Trade Forum ላይ ባደረገው ተሳትፎ የሀገራችንን የኢንቨስትመንትና ንግድ ዕድሎች አስተዋውቋል፡፡ ልዑካን ቡድኑ በቆይታው በሀገራችን አማራ ክልል በፋርማሲውቲካል መስክ ተሰማርቶ በከፍተኛ ግብር ከፋይነት የፕላቲኒየም ደረጃ ለተከታታይ ሁለት ዓመታት ተሸላሚ የነበረ Humanwell Pharmaceutical Co.,Ltd. ኩባንያ ጉብኝት በማድረግ በሀገራችን ያለውን ኢንቨስትመንት በሚያስፋፋበት ሁኔታ ላይ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ክቡር አምባሳደር ደዋኖ ከድር ከWuhuan Engneering group ምክትል ፕሬዚዳንት Mr. Wang Jiayi ጋር ኩባንያው የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ በሀገራችን በሚጀምርበት ሁኔታ ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ፣ ከስብሰባው በኃላ ሥራ ለመጀመር የሚያስችል የአዋጭነት ጥናት የሚያደርግ ልዑካን ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ተልኳል፡፡ በተጨማሪም በተለያዩ ኢንቨስትመንት እና ንግድ ሥራ ላይ ከተሰማሩ Hubei International Economic and Technical Cooperation Co., Ltd. እንዲሁም በግብርና ፕሮሰስግ መስክ ከተሰማራው Hubei Lianfeng Overseas Agricultural Development Group Co., Ltd. ኃላፊዎች ጋር በሀገራችን በኢንቨስትመንትና ንግድ መስክ ባሉት ዕድሎች ዙሪያ ውይይቶች ተካህደዋል፡፡
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook