በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከGrand World Investment Holding Group ኩባንያ ፕሬዚዳንት ጋር ውይይት አደረገ፣
===================================
በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምክትል መሪ ክቡር አምባሳደር ደዋኖ ከድር ከGrand World Investment Holding Group ኩባንያ ፕሬዚዳንት Mr. Wenguang Liu ጋር በኢትዮጵያ በማኑፋክቸርንግ መስክ ኢንቨስት በሚያደርጉበት ሁኔታ ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡ ኩባንያው በመስኩ በተለይም በፋርማሲውቲካል፣ በአግሮ-ፕሮሰስንግ፣ በኤልክትሪክ መኪኖች መገጣጠም እና ቻርጂንግ ስቴሽኖች በመዘርጋት መስክ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ፕሬዚዳንቱ የገለጹ ሲሆን፣ ከግንቦት 1 እስከ 5 አዲስ አበባ በሚካሄድ “ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖና ባዛር” ላይ Mr. Wenguang Liu ለመሳተፍ ዝግጅት እያደረጉ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ክቡር አምባሳደሩ ኩባንያው በመስኩ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ኤምባሲው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው አረጋግጠዋል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook