በቻይና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር ተፈራ ደርበው ከChina Machinery Engineering Corporation ዋና ሀላፊዎችን ዛሬ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ውይይት አድረገዋል፡፡ ይህ ትልቅ ካምፓኒ በአገራችን የፖታሽ ማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ፍላጎት ያለው ሲሆን፣ በዘርፉ ትልቅ አቅም ያለውና በግብርናው ዘርፍ ያለውን የማዳበሪያ እጥረት የሚቀርፍ መሆኑ ተነስቷል፡፡
በውይይቱም የካምፓኒው ስራ መጀመር የአገራችን የግብርና ዘርፍ ማነቆ ከመፍታቱም በላይ አገራችን በምግብ እራስን ለመቻል በምታደረገው ጥረት የጎላ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ክቡር አምባሳደር ገልፀውላቸውዋል፡፡
በዚህም ሚሰዮኑ ለካምፓኒው አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ በፍጥነት ወደ ስራ የሚገባበትን መንገድ እናመቻቻለን ብለዋል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook