በቤጅንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከቻይና-አፍሪካ የኢኮኖሚ እና ንግድ ጉዳዮች አስተባባሪ ኮሚቴ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሄደ፣
የሚሲዮኑ ምክትል መሪ ክቡር አምባሳደር ደዋኖ ከድር በChina-Africa Economic and Trade Working Committee ፕሬዚዳንት Mr. Huang ከተመራ ልዑካን ቡድን ጋር በኤምባሲው ተገናኝተው ውይይት አካሂደዋል፡፡ በውይይታቸውም በሀገራችን ቅድሚያ በሚሰጥባቸው ኢንቨስትመንት መስኮች፣ በንግድ እና በቱሪዝም ዘርፍ ያሉ ዕምቅ ዕድሎችን ለማስተዋወቅ የሚረዱ ፎረሞችን በጋራ በተለያዩ ከተሞች ለማዘጋጀት፣ በቡድን በኢትዮጵያ የቅድመ-ኢንቨስትመንት ጉብኝት የሚያደርጉ ልዑካን ቡድኖችን በጋራ ለማስተባበር እንዲሁም ከግንቦት 1 እስከ 5 ቀን 2016 ዓ.ም በሀገራችን በሚካሄድ ‘’ ኢትዮጵያ ታምርት ኤክፖና ባዛር’’ ላይ የቻይና ባለሀብቶች በንቃት እንዲሳተፉ በጋራ ለማስተባበር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook