በ”Coffee Month of Asian Game, Hangzhou” ላይ ተሳትፎ ተደረገ
=========================================
በቻይና ቤጂንግ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በቻይና ጄጃን ክፍለ ሀገር ሀንጆ ከተማ ከሴፕቴምበር 21 እስከ ኦክቶበር 10 ቀን 2023 በሚካሄደው የCoffee Month of Asian Game, Hangzhou” ላይ ሴፕቴምበር 21 እና 22 የኢትዮጵያ ቡና ፕሮሞሽን ቀን ተብሎ በተሰየመበት መሰረት ተሳትፎ ተደርጓል::
የፕሮግራሙ ዓላማ በቻይና በተለይም በወጣቱ ዘንድ ውዴታውእየጨመረ የመጣውን ቡና መጠጣት ተከትሎ የቡና አብቃይ አገራትን የቡና ዓይነት ለማስተዋወቅ ታልሞ የተዘጋጀ ነው።
በፕሮግራሙ ላይ ኤምባሲያችን የኢትዮጵያን ቡና ለቻይና ቡና ወዳዶች፣ ለካፌ ባለቤቶችና በቡና ገቢ ንግድ ላይ ለተሰማሩ ድርጅቶች የማስተዋውቅና በፓናል ውይይት ላይ በመሳተፍ ለተነሱ ጉዳዮች ማብራሪያ በመስጠት ተሳትፎ የተደረገ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ የተሳተፉ አካላትም የአገራችንን ቡና በተመለከተ አድናቆታቸውን ገልፀዋል። ጎን ለጎንም በተዘጋጀው የቡና ኤግዚቢሽን ላይ ኤምባሲያችንን ጨምሮ የአገራችን ኤክስፖርተሮችም ተሳትፎ እያደረጉ ሲሆን ባህላዊ የቡና አፈላል ስነስርአትን ማስተዋወቅ ተችሏል።
Ethiopian Embassy in Beijing has Participated in “Coffee Month of Asian Game, Hangzhou”
===========================================
The Embassy of Ethiopia in Beijing, China is participating in the “Coffee Month of Asian Game, Hangzhou” underway from September 21 to October 10, 2023 in the city of Hangzhou, Zhejiang Province, China. September 21 and 22 are nominated as Ethiopian coffee promotion days by the organizers. Following the increasing consumption of coffee in China, the program aims to promote the coffees of coffee-growing countries. In the program, the embassy was able to introduce Ethiopian coffee to Chinese coffee lovers, café owners and companies involved in the coffee business, and also participated on panel discussion.
Besides, our Embassy and the exporters of our country are participating in the coffee exhibition. Traditional coffee brewing ceremony has been introduced.

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook