በ”Global Food and Beverage Forum” ላይ ተሳትፎ ተደረገ
በቻይና ቤጂንግ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በቻይና ሀይናን ክፍለ ግዛት ቦአኦ (Boao) ከተማ ከሴፕቴምበር 15 እስከ 17 2023 በተዘጋጀ የGlobal Food and Beverage Forum” ላይ ተሳትፎ እየተደረገ ነው:: የፎረሙ ዓላማ የምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪው በኮቪድ 19 ካጋጠመው ጉዳት በኋላ መልሶ በማገገም በአገራት መካከል የኢኮኖሚ ትስስሩ የሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ አብሮ መስራት እንዲቻል ታስቦ የተዘጋጀ ነው። በፎረሙ ላይ ኤምባሲው የኢትዮጵያ ወጪ የግብርና ምርቶች ማስተዋውቅ የተቻለ ሲሆን ወደቻይና የምንልካቸውንም ምርቶች የተገኙ ዕድሎችን በመጠቀም ከጊዜ ወደጊዜ አየጨመረ መምጣቱ ተገልፇል።
ከፎረሙ ጎን ለጎን በተካሄደው ኤግዚቢሽን ላይ ከሀይናን እና ከተለያዩ የቻይና ከተሞች ለመጡ ለከተማ አስተዳዳሪዎች፣ ለማህበራት፣ ለንግድ ድርጅት ተወካዮች የኢትዮጵያ የወጪ ምርቶች ለዕያታ በማቅረብ ማስተዋወቅ የተቻለ ሲሆን በቀጣይ ግብይት ለመፈፀም ፍላጎት ላሳዩ የማህበራትና የንግድ ተቋማት ተወካዮች መረጃዎችን እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል።
Ethiopian Embassy in Beijing has Participated in “Global Food and Beverage Forum”.
The Ethiopian Embassy in China, Beijing has participated in the Global Food and Beverage Forum organized in China, Hainan Province, Boao city from September 15 to 17, 2023. At the forum, the embassy promoted agricultural export products and that the products we export to China have increased from time to time by using the available opportunities to the participants.
At the exhibition held alongside to the forum, gives big chance to promote Ethiopian export products to city managers, associations, and business representatives from Hainan and various Chinese cities.