በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ በውሃን ከተማ በተካሄደው ቻይና አፍሪካ ኢኖቬሽን ኮፕሬሽን እና ዲቨሎፕመንት ፎረም ላይ ተሳትፎ አደረገ።
=========================================================
በፎረሙ ለይ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያና ቻይና ወዳጅነት በ2017 ወደ ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂያዊ ትብብር ያደገ መሆን እና ኢትዮጵያ ለብዙ የቻይና ኢንቨስተሮች ተቀዳሚ ምርጫ መሆንዋን አንስተው አሁንም ባለው ምቹ የኢንቨስትመንት
አማራጭ ተጠቅመው ኩባንያዎቹ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
በፎረሙ ላይ የተገኙት የባህር ዳር ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኝ ከሃንጆ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ጋር በጋራ ለመሰማራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል::