የቻይና አፍሪካ የትብብር ማዕቀፍ (FOCAC) አንዱ አካል የሆነው የቻይና-አፍሪካ ንግድ እና ኢኮኖሚ ኤክስፖ እ.ኤ.አ ከጁን 28 እስከ ጁላይ 2 ቀን 2023 ለሶስተኛ ጊዜ በቻንግሻ ከተማ እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን አገራችንን ጭምሮ በርካታ አፍሪካ አገራት በመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ደረጃ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛል።
ከኤክስፖው ጎን ለጎን በቻይና የማሽነሪ አምራች እና ሻጮች የንግድ ምክር ቤት እና የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት አዘጋጅነት በተካሄድው የአፍሪካ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ፕሮሞሽን ኮንፍረንስ ላይ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዳንኤል ተሬሳ ተገኝተው ስለ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ምቹ የኢንቨስትመንት እድሎች ገለጻ አድረገዋል።
በፕሮሞሽን መደረኩ ላይ ባለፉት አስርት አመታት መንግስት ዘመናዊ የኢንዱስትሪ ፓርኮች በመገንባት ወደ ስራ መግባቱና እና በአሁን ወቅት በመንግስት እና በግል ባለሃብቶች የሚለሙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች አገሪቱን ምቹ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መዳረሻ እንድትሆን ጉልህ አስተዋዕጾ እያበረከቱ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ምክትል ኮሚሽነሩ አክለውም መንግስት የውጭ ባለሃብቶች በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገቡ የሚያስችል የተቀላጠፈ የአንደ-መስኮት አግልግሎት አስጣጥን ተግባራዊ በማድረግ ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢን መፈጠር ረገድ ከፍተኛ ሚና እያተጫወተ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የአገራችን ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለውጭ ባለሃብቶች የሚሰጡትን ሰፊ የኢንቨስትመንት እድሎችን በሰፊው በማብራርት የቻይና ኩባንያዎች በአገራችን የተመረጡ የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ በመሰማራት ከዚህ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።
በፕሮሞሽን መድረኩ ላይ የተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት የቻይና ቀርንጫፍ ጽ/ቤት በአገራችን እንዲገቡ ድጋፍ ያደረገባቸውን የግብርና መቀናባባሪ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ምቹ እድሎች በማብራራት የቻይና ኩባንያዎች በፓርኮች በመንግባት ኢንቨስት እንዲያደርጉ አበራርታተዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook