በቻይና የኢፌዲሪ አምባሳደር ከቡር ተፈራ ደርበው ጓንዶንግ ከክ/ሀገር የውጭ ጉዳይ ቢሮ ዳ/ጄኔራል Mrs.LiuChenzi ጋር በኦንላይን ተወያይተዋል፡፡ክቡር አምባሳደሩ ቻይና የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ አጋር መሆኗን ጠቁመው የሁለቱ አገራት ግንኙነት ከጊዜ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡
በቅርቡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቻይና በረራ የጀመረበትን 50ኛዓመት በቤጂንግ በድምቀት መከበሩን አስታውሰው በድህረ ኮቪድ ወረርሽኝጓንጆን ጨምሮ በሌሎች የቻይና ከተሞችም የበረራ ቁጥሩ መጨመሩን ይህም ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑንና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ተናግረዋል፡፡አምባሳደር ተፈራ አያይዘውም ጓንዶንግ በርካታ ባለሃብት ያለበት ከፍለሃገር እንደመሆኑ መዋዕለንዋያቸውን በኢትዮጵያ በማዋል የጋራ ተጠቃሚነታቸውን ማጎልበት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም ክቡር አምባሳደር ከሚያዚያ 18-20/2015 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በሚካሄደው የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ የጓንዶንግ ባለሃብቶች እንዲሳተፉና በአገሪቱ ያሉትን የኢንቨስትመንት እድሎች ይበልጥ እንዲገነዘቡ ለማድረግ የውጭ ጉዳይ ቢሮው በመቀስቀስና በማስተባበር ረገድ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪአቅርበዋል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook