በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ በDezhou ከተማ የቢዝነስ ፎረም አካሄደ፣
=================================
በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከDezhou ከተማ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ጋራ በመተባበር እ.ኤ.አ. ኤፕሪል 24 ቀን 2024 በDezhou ከተማ የኢንቨስትመንትና ንግድ ማስተዋወቂያ ፎረም አዘጋጅቷል፡፡ በፎረሙ በክቡር ምክትል ሚሲዮን መሪ አምባሳደር ዳዋኖ ከድር የተመራ የኤምባሲያችን ልዑካን ቡድን ተሳታፊ የሆነ ሲሆን በከተማው በኩል የከተማውን ከንቲባ ጨምሮ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊዎች፣ የከተማው ንግድ ቢሮ ኃላፊዎች፣ የከተማው የCCPIT ኃላፊዎች እና በተለያዩ ኢንቨስትመንት መስኮች የተሰማሩ ባለሀብቶች ተሳትፈዋል፡፡፡

በመድረኩ ክቡር የሚሲዮኑ ምክትል መሪ አምባሳደር ዳዋኖ ከድር አጠቃላይ በሀገራችን እና በቻይና መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት በተመለከተ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪም የሀገራችን የኢንቨስትመንትና ንግድ ዕድሎች በተመለከተ በሀገራችን ቅድሚያ በሚሰጥባቸው የኢንቨስትምንትና ንግድ መስኮች ላይ ትኩረት በማድረግ ጹሑፍ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በከተማውም በኩል የከተማው ከንቲባ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ አጠቃላይ በከተማው እና በሀገራችን መካከል ያለውን መልካም ግንኙነት በተመለከተ ያነሱ ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪ በከተማው ንግድ ቢሮ ኃላፊ እና ከCCPIT ኃላፊ አጠቃላይ ከተማውን የኢኮኖሚ አቅም በሚመለከት እንዲሁም ከሀገራችን ጋር ያለውን የኢንቨስትመንትና ንግድ ግንኙነት በተመለከተ መወያያ ጹሑፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡

በክቡር አምባሳደር ዳዋኖ ከድር የተመራ የኤምባሲው ልዑካን ቡድን በፎረሙ ከተሳተፉ ባለሀብቶች መካከል የተወሰኑ በሶላር ኢኔርጂ እና በአግሮ-ፕሮሰስንግ መስክ የተሰማሩ ኩባንያዎች በመጎብኘት ከኩባንያዎቹ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook