በቻይና ኩንሻን ከተማ በ”China Kunshan International Fair for Coffee Industry 2024 ላይ ተሳትፎ ተደረገ
=============================================
ከሜይ 16 እስከ ሜይ 19 ቀን 2024 በቻይና ኩንሻን ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የ “China Kunshan International Fair for Coffee Industry 2024 ላይ ሚሲዮናችን ተሳትፎ በማድረግ ላይ ይገኛል። በመክፈቻ መርሀ ግብር ላይ የከተማዋ ከንቲባና ሌሎች የቻይና መንግስት ተወካዮች የተገኙ ሲሆን በወቅቱም ሚሲዮናችን በመሳተፍ የአገራችንን ቡና ማስተዋወቅ ተችሏል። በተመሳሳይ በዕለቱ በተካሄደው የ”Coffee origin Forum” ላይ የኢትዮጵያ ቡና ላኪ ዎች ማህበር ስራ አስኪያጅ የኢትዮጵያ ቡና ግብይት በአጠቃላይ በዓለም ገበያ ላይ እና በተለይም በቻይና እያደገ የመጣውን አፈፃፀም በሚያሳይ መልኩ ገለፃ አድርገዋል።
በተጨማሪም እየተካሄደ ባለው ኤግዚቢሽን ላይ በማህበሩ አስተባባሪነት ቡዝ የተያዘላቸው 27 እና በግላቸው ቡዝ የያዙ 20 በድምሩ 47 የአገራችን ቡና ላኪዎች ተሳትፎ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ይህም ተሳትፎ ለአገራችን ቡና ላኪዎች አቅም ካላቸው የቻይና ቡና ገዥዎች ጋር ትስስር ለመፍጠር አመቺ በመሆኑ ሚሲዮኑ የድጋፍና ክትትል ስራ በመስራት ላይ ይገኛል። ባህላዊ የቡና ስርአትን የማሳየትና የቡና ማስቀመስ ስራም ተከናውኗል።