ማሳሰቢያ

በቻያና እና በአካባቢዋ የከፍተኛ ትምህርት በመከታተል ላይ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በሙሉ

ተማሪዎች በውጭ አገራት ትምህርታቸውን ተከታትለው ካጠናቀቁ በኃላ ተገቢውን የሰነድ ማረጋገጥ ሂደት ሳያጠናቅቁ አገር ቤት እየተመለሱ ለተጨማሪ እንግልትና ወጪ እየተዳረጉ መሆኑን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንፃላ ጉዳዮች ዳ/ጄ በፃፈልን ደብዳቤ አሳውቋል። በዚሁም መሰረት ተማሪዎች ትምህርታችሁን ካጠናቀቃችሁ በኃላ

  1. የትምህርት ማስረጃችሁን ከተማራችሁበት አገር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወይም ሌላ የሚመለከተው ተቋም እንዲረጋገጥ ማድረግ በቻይና የ Notary office እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር (ለፕሮቪንሶች foreign affairs office)
  2. በቻይና የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ማስረጋገጥ
  3. ወደ አገር ቤት ስትመለሱ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንፃላ ጉዳዮች ዳ/ጄ ማስረጋገጥ ይኖርባችል።

ይህ ካልሆነ ግን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ቁጥጥር ባለስልጣን የአቻ ግመታ መሰራት እና ከውጭ አገር የሚገባ የትምህር ማስረጃ በአገር ውስጥ ጥቅም ላይ እንዲውል ማረጋገጫ መስጠት እንደማይችል አሳውቋል።

በመሆንም ተማሪዎች ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተጠቀሱትን ሄደቶች ወደ አገርቤት ከመመለሳችሁ በፌት በማጠናቀቅ ከአላስፈላጊ እንግልትና ተጨማሪ ወጪ እንድትድኑ ከወዲሁ እናሳስባለን።

284

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook