በ “2024 BRICS Women’s Leadership Forum” ላይ ተሳትፎ ተደረገ
≈≈=≈===============================

በቤጂንግ ከተማ በቻይና ዓለም አቀፍ የንግድ ምክር ቤት አስተባባሪነት በተዘጋጀ በ “2024 BRICS Women’s Leadership Forum” ላይ ተሳትፎ ተደረገ።

በፎረሙ ላይ የBRICS አባል አገራት የሴቶች አደረጃጀት ሀላፊዎች ተሳትፎ ያደረጉ ሲሆን ፎረሙ ከተመሰረተበት እ.አ.አ. ከ2020 ጀምሮ በሴቶች ሁለንተናዊ የኢኮኖሚና የማህበራዊ እመርታዎችን እያሳየ የመጣ መሆኑንና በቀጣይም ሴቶችን በማብቃት የሴት ስራ ፈጣሪዎችን ቁጥር ማበራከትና በየዘርፉ አስተዋፅዋቸው እየላቀ እንዲመጣ እንደሚሰሩ አፅእኖት በመስጠት ገልፀዋል።

ኤምባሲያችንም የBRICS አባል መሆናችን በቀጣይ በጋራ ለመስራት አስቻይ በመሆኑ የፎረሙን ዕድል በመጠቀም የአገራችን ሴቶች ተሳትፎ የምናጎለብት መሆኑ ሀሳብ ቀርቧል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook