በቤጅንግ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ በZhejiang Gongshang University ምክትል ዲን ከተመራ ልዑክ ጋር ውይይት አደረገ፣
==============
በቤጂንግ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ ምክትል መሪ ክቡር አምባሳደር ደዋኖ ከድር በZhejiang Gongshang University ምክትል ዲን Dr. Xiaofei Zhou ከተመራ ልዑካን ቡድን ጋር በኤምባሲው ውይይት አድርገዋል፡፡ በልዑካን ቡድኑ 4 በማኑፋክቸሪንግ መስክ የተሰማሩ ኩባንያዎች ኃላፊዎች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን፣ ክቡር አምባሳደሩ Zhejiang Gongshang University ከሀገራችን ዩኒቨርሲትዎች ጋር ጉድኝት በሚፈጥርበት እንዲሁም በልዑካን ቡድኑ የተሳተፉ ኩባንያዎች በመኪና ማምረት፣ በጨርቃጨርቅ እና በአግሮ-ፕሮሰስንግ መስኮች በሀገራችን ኢንቨስት በሚያደርጉበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ያደረገ ውጤታማ ውይይት አድርገዋል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook